የአባልነት መመሪያ

አስቀድሞ ተመዝግበዋል?

አንዴ ምዝገባዎ ከተፈፀመ በኋላ, ከ AHSM አባልነትዎን ለማግበር የሚያስችል ኢሜይል ይደርስዎታል። እንዲሁም በየአመቱ አባልነትዎን ለማደስ ጊዜው ሲደርስ ኢሜይል እንልክልዎታለን።

አዲስ አባላት

እባክዎ ከዚህ በታች የሚገኘውን የ AHSM የአባልነት ፖሊሲ ያንብቡ, ከዚያም በዚህ ገፅ መጨረሻ ቅፅ ላይ ይሙሉ።
ቅጹን ከሞሉ በኋላ ለእርስዎ የአባልነት መታወቂያ ቁጥር እና የአባልነት ክፍያዎን እንዴት እንደሚያደርጉ መመሪያዎችን በኢሜይል  ይደርስዎታል።

የአባልነት ፖሊሲ

ስለ አባልነት ፖሊሲ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ።

የአባልነት ዓይነቶች:

ሁለት የአባልነት አይነቶች አሉ፤ አባል እና መራጭ አባል። አባል ወይም መራጭ አባል ለመሆን ከታች በዘርፉ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ማሟላት ያስፈልጋል።

አባል

  • ማንኛውም በድርጅቱ ዓላማ የሚያምን ግለሰብ ለአባልነት ማመልከት ይችላል።
  • የመምረጥ መብት ለማግኘት ግን ከታች የተዘረዘሩትን የመራጭ አባል መሥፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።

መራጭ አባል

  • መራጭ አባል ለመሆን ለአንድ አመት የድርጅቱ አባል በመሆን የአባልነት መዋጮ በመክፈል እና ንቁ ተሳትፎ በማበርከት መቆየት ያስፈልጋል።
  • አባል ለመሆን የሚያመለክተው ግለሰብ ቢያንስ በእናቱ ወይም በአባቱ ወገን የአማራ ተወላጅ መሆን አለበት።

የምክር ቤት ወይም የስራ አስፈጻሚ አባል መሆን

የምክር ቤት ወይም የስራ አስፈጻሚ አባል ሆኖ ለመመረጥ ከታች የተዘረዘሩት በሙሉ ማሟላት ያሰፈልጋል።

  • መራጭ አባል ሆኖ ለሃያአራት(24) ወራት መቆየት
  • በእናት እና በአባት በሁለቱም ወገን አማራ መሆን
  • ስለ ንቁ ተሳትፎው ቢያንስ ከወቅቱ ካሉት አምስት(5) የቦርድ ወይም የስራ አስፈጻሚ አባላት ምስክር ማቅረብ

ለአባልነት ማመልከት

ከሚከተሉት በአንዱ መልክ አባል ለመሆን ማመልከት ይቻላል።

  • እዚህ ድህረ ገጽ ላይ የሚገኘውን የአባልነት ማመልከቻ ቅጽ ሞልቶ እዚሁ ላይ በመላክ
  • የአባልነት ማመልከቻ ቅጹን አትሞ በእጅ ከሞሉ በኋላ በሚከተለው አድራሻ በመላክ

Amhara Heritage Society of Minnesota 1821 University Ave W, Suite S-340, MN 55104

  • የአባልነት ማመልከቻ ቅጹን አትሞ በእጅ ከሞሉ በኋላ amharamn@gmail.com በኢሜይል በመላክ

አባላትን የመቀበል ሂደት

  • አባል ለመሆን የሚፈልገው ግለሰብ የአባልነት ማመልከቻ ቅጹን ያስገባል
  • የድርጅቱ የአባላት ምልመላ ክፍል ሃላፊ ማመልከቻ መግባቱ ይነገረዋል
  • የድርጅቱ የአባላት ምልመላ ክፍል ሃላፊ ከአመልካቹ ጋር በአካል ተገናኝቶ ለመገናኘት ቀጠሮ ይይዛል
  • የድርጅቱ የአባላት ምልመላ ክፍል ሃላፊ ከአመልካቹ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ለአባልነት አጽዳቂ ኮሚቴ ያቀርባል
  • የአባልነት አጽዳቂ ኮሚቴው ወሳኔ ይሰጣል
  • የድርጅቱ የአባላት ምልመላ ክፍል ሃላፊ ወሳኔውን ለአመልካቹ ያሳውቃል
  • ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ አመልካቹ የአባልነት ከፍያውን ከፍሎ አባል ይሆናል

የአባልነት ከፈያን መክፈል

  • ማንኛውም በአባልነት የተመዘገበ አባል የአባልነት ክፍያውን እዚህ ድህረ ገጽ ላይ ወይም ቼክ በሚከተለው አድራሻ በመላክ መክፈል ይችላል

Amhara Heritage Society of Minnesota 1821 University Ave W, Suite S-340, MN 55104

  • አዲስ አባል ለመሆን ያመለከቱ ገለሰቦች ማመልከቻቸው ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ከላይ ከተጠቀሱት በአንዱ መንገድ የአባልነት ክፍያቸውን መክፈል ይችላሉ።

አዲስ የአባልነት ምዝገባ